አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran

አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran

BunnyCode
Apr 27, 2022
  • 5.0 and up

    Android OS

À propos de አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran

Amharic translation of the Holy Quran by Sheikh Mohammed Sani Habib and Sheikh Saeed Mohammed Sadiq

ከሃምሳ ዓመት በፊት በሸኽ ሙሐመድ ሳኒ ሃቢብ እና በሸኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ የቀረበው የክቡር ቅዱስ ቁርኣን የአማርኛ ትርጉም፤ እንሆ በወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ድምፅ ተዘጋጅቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቅዱስ ቁርኣንን ትርጉም ማድመጥ ለሚፈልጉ አመቺ ኾኖ ቀርቧል።

ይህ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ መግቢያውና ሙስሊሞች በአጠቃላይ ቁርአን ከእግዚአብሔር መጣ የሚል እምነት እንዳላቸው የሚናገር ነው፡፡ ሙስሊሞች በሙሉ ያላቸው ይህ እምነትና መረዳት በሐቀኛ ምርመራ በመመሥረት የቁርአን ምንጭ ምንነት መገለጡ መከተል ያለባቸውን አሁኑኑ እንዲያስቡበት በጣም እንደሚረዳቸው ይታመናል፡፡

ቅዱስ ቁርአን ወይንም ቁርአን) የመሃከለኛዉ አለም የእስልምና የቅዱስ መጽሃፍ ወይም የእምነት ጽሁፍ ነዉ፣ በዚህም ትምህርት ይህ ጽሁፍ የመጣዉ በአላህ ፈቃድ ቃሉን በጂብሪል አማካኝነት ለነብዩ ሙሀመድ የወረደ የአላህ ቃል ነው። ቅዱስ ቁርአን ለመጀመርያ ጊዜ በአረብኛ ነበር የተጻፈዉ። አላህ ለቁራን ቃል ገብቶለታል እሱም ማነም ሰዉ መበረዝ እንደማይችል እና ማነም ሰዉ ቃሉን ቀይሮ ህጉን ሊአሳስት እንደማይችል ነዉ። አላህ ሁልጊዜም ከመበረዝ የሚጠብቀዉ በአለም ላይ ያለ ብቸኛው መጽሃፍ ነዉ። ይሀም በአማርኛ የተተረጎመ ቁርዓን ነዉ።

ቁርአን ሰዎች እና አጋንንት እንኳ ቢሰበሰቡ የሱብ ተመሳሳይ አንቀጽ ወይም አረፍተ ነገር ማምጣት ይችሉ እንደሆነ ይሞክሩ በማለት ተአምረኛነቱን እና እውነተኛነቱን አረጋግጧል። ቁርአን ከመበዘረዝ እና ከመከለስ የጠራ ነው። እንደዚህም የሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ እንደሆነ ሳይበረዝ እና ሳይከለስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቆያል፤ ምክንያቱም አላህ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል ስለገባለት ቁርአንን በተመለከተ ሙስሊሞች ምንም አይነት ልዩነት የለባቸውም። በአረብኛ ተጽፎ አንድ ቃል ይቅርና አንድ ፊደል እንኳ ሊጨመር ቢችል ወይም ቢቀነስ በቀጥታ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል። የሰው ልጆች በዚህ ምድርም ይሁን በመጭው አለም ሰላም እና እርጋታ ከፈለጉ ሙስሊም ሆነው በቁርአን መመራት አለባቸው የሚል ትምህርት ያቀርባል።

የድምፅ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ በዚህ መተግበሪያ እስኪጫን ድረስ፤ ለጊዜው ሱረት አል ፋቲሃን ጨምሮ ከሱረቱ አን ናስ እስከ ሱረቱ አን ነበእ (አንድ ጁዝ) የትርጉም ድምፅ ሥራው ያለክፍያ ቀርቧል።

በዚህ አጋጣሚ እንደ አላህ ፈቃድ ሥራችንን ከእንከን የጠራ ለማድረግ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና ጥንቃቄ ጥረት ያደረግን ቢኾንም፤ ሰዎች ነንና ልንሳሳት እንደምንችል እናምናለን። በመኾኑም ይህ ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የቅዱስ ቁርአን ትርጉም እንደመኾኑ በማድመጥም ኾነ በማንበብ ሂደት ውስጥ የሚታያችኹን ክፍተት እንድተጠቁሙን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

ይህን ታላቅ ሥራ አኑረው ያለፉ አባቶቻችንንና ከህትመት እስከ ስርጭት የደከሙ ወንድምና እህቶችን ኹሉ ለሠሩት መልካም ሠራ ምንዳውን ያብዛላቸው። እኛንም በሰማነው የምንጠቀም ያድርገን። አሚን!!

Voir plus

What's new in the latest 1.0.0

Last updated on Apr 27, 2022
Minor bug fixes and improvements. Install or update to the newest version to check it out!
Voir plus

Vidéos et captures d'écran

  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran Affiche
  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran capture d'écran 1
  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran capture d'écran 2
  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran capture d'écran 3
  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran capture d'écran 4
  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran capture d'écran 5
  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran capture d'écran 6
  • አል-ቁርዓን ትርጉም - Amharic Quran capture d'écran 7
APKPure icône

Téléchargement super rapide et sûr via l'application APKPure

Un clic pour installer les fichiers XAPK/APK sur Android!

Téléchargement APKPure
thank icon
We use cookies and other technologies on this website to enhance your user experience.
By clicking any link on this page you are giving your consent to our Privacy Policy and Cookies Policy.
Learn More about Policies