ነቅረእ - 02 የዐረብኛ (ቁርኣን) ንባብ መማሪያ (Neqra 02)

  • 99.6 MB

    Dimensione

  • Android 4.1+

    Android OS

Informazioni su ነቅረእ - 02 የዐረብኛ (ቁርኣን) ንባብ መማሪያ (Neqra 02)

Nukemt è un apache in grado di leggere copioni amarico e arabo che conoscono l'alfabeto arabo

ነቅረእ 02 የዐረብኛ (ቁርኣን) ንባብ መማሪያ የሞባይል አፕልኬሽን የነቅረእ 01 የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ የሞባይል አፕልኬሽን ቀጣይ ክፍል ሲሆን፣ አማርኛን በአግባቡ ማንበብ ለሚችሉና የዐረብኛ ፊደላትን በደንብ ለይተው ለሚያውቁ የዐረብኛ (ቁርኣን) ንባብን ቀላል በሆነ መንገድ የሚያስተምር ዘመናዊ የሞባይል አፕልኬሽን ነው።

ይህ አፕልኬሽን በአጠቃላይ በ 13 ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ነው። እያንዳንዱ ክፍልም በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ነው።

አፕልኬሽኑ በቅድሚያ የአማርኛ ፊደላት እንቅስቃሴን በ ክፍል 1 ያስተምራል።

በመቀጠልም በክፍል 2፣ 3፣ 4 እና 5፣ የዐረብኛ ፊደላትን (ቃላትን) በአራቱ የዐረብኛ አናባቢ ምልክቶች (ፈትሐ፣ ከስራ፣ ዱማ እና ሱኩን) በመጠቀም ከአማርኛ ፊደላት የድምፅ እንቅስቃሴ ጋር በማዛመድ፣ ቀላል በሆነ መንገድ የማንበብ ት/ት ይሰጣል።

በክፍል 5፣ 6 እና 7 ደግሞ በሶስቱ የዐረብኛ አናባቢ ምልክቶች (በፈትሐ፣ በከስራ፣ እና በዱማ) የተነበቡ ድምፆች ሳብ አድርጎ የማንበብ ት/ት ይሰጣል።

በክፍል 8፣ 9 እና 10 ደግሞ ሶስቱ የዐረብኛ አናባቢ ምልክቶች (በፈትሐ፣ በከስራ፣ እና በዱማ) ተደራርበው ሲመጡ በነጠላ ከሚሰጡት ድምፅ ላይ "ን" ድምፅን በመጨመር የማንበብ ት/ት ይሰጣል።

በክፍል 12 የዐረብኛ ፊደላትን ድምፆች የሽዳ (ማጥበቂያ) ምልክትን በመጠቀም አጥብቆ የማንበብ ት/ት ይሰጣል።

በመጨረሻም በክፍል 13 ከቁርኣን የተወሰኑ አንቀፆችን የማንበብ ልምምድ ይደረጋል።

ሁሉም ክፍሎች አራት አራት ንዑስ ክፍሎች ያሏቸው ሲሆን፣ እነሱም

መማሪያ፣ አጋዥ ቪዲዮ፣ መልመጃ እና ፈተና ናቸው። ከክፍል ክፍል ማለፍ የሚቻለው ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በመመለስ ነው።

Mostra AltroMostra meno

What's new in the latest 1.0

Last updated on 2019-04-19
- Improved Broadcast Notification
- Bug Fixes

Vecchie versioni di ነቅረእ - 02 የዐረብኛ (ቁርኣን) ንባብ መማሪያ (Neqra 02)

Download super veloce e sicuro tramite l'app APKPure

Basta un clic per installare i file XAPK/APK su Android!

Scarica APKPure