ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

  • 9.6 MB

    Bestandsgrootte

  • Everyone

  • Android 4.0+

    Android OS

Over ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና በቅብዐት እምነት መካከል ያለውን ልዩነት የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው.

«ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ» በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ዶግማ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ከ፲፪ መጻሕፍት በላይ ተካተውበት የቀረበ የመጻሕፍት መድብል ነው።

ይህ የመጻሕፍት መድብል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትርጓሜ ሊቃውንት የተራቀቁባቸውን እና የተጠበቡባቸውን ሲወርዱ ሲወራረዱ ለእኛ የደረሱ የትርጓሜ መጻሕፍት የተካተቱበት ነው። በሦስት ዐበይት ክፍሎች የተመደቡ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ያካተተው ይህ መድብል ምክርና ተግሳጽንም የያዘ ስለሆነ ብዙዎች እንደሚወዱት ተስፋ እናደርጋለን። በአዘጋጁ ታትመው የቀረቡና እና ለኅትመት ዝግጁ የሆኑ መጻሕፍትም የተካተቱበት ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል። በአዘጋጁ ከቀረቡ መጻሕፍት መካከል በቅብዐት ምንፍቅና አማኞች ለተጻፉ መጻሕፍት ተገቢ ምላሽ የተሰጠባቸውን «ደብረ አሚን - የሃይማኖት ተራራ» እና «ፍኖተ ጽድቅ - የእውነት ጎዳና» አካተናል። ከዚህ በተጨማሪም አዘጋጁ የጻፋቸው የተለያዩ ወጎች ፣ ትምህርቶችና ግጥሞችም ምክርና ተግሳጽን በስፋት አካተው ቀርበውበታል። ከእግዚአብሔር ለምን እንርቃለን? እግዚአብሔርስ ከእኛ ለምን ይርቃል? የሚመራ መሠረታዊ ጥያቄ የሚመልስ እና ወደ ንስሐ የሚመራ «ለምን ርቀህ ቆምህ?» የተሰኘው የአዘጋጁ መጽሐፍም በዚሁ መድብል ውስጥ የተካተተ ነው። እነዚህ የአዘጋጁ መጻሕፍት ገበያ ላይ የማይገኙ መሆናቸው ይህን መተግበሪያ ልዩ ያደርገዋል።

ይህ መተግበሪያ በተጨማሪነት ቤተ ክርስቲያናችን ከዓመት እስከ ዓመት የምትገለገልባቸውን ድንቅ መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውንና መጽሐፈ ስንክሳርን ያካተተ ነው።

ይህ መተግበሪያ የያዛቸው መጻሕፍት ዝርዝር

፩. የአንድምታ ትርጓሜ ክፍል

- የጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ።

-የውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።

- የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።

- የአራቱ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ።

፪. የአዘጋጁ መጻሕፍት ክፍል

- ደብረ አሚን

- ፍኖተ ጽድቅ

- ለምን ርቀህ ቆምህ?

- አማኞችን ማጽናትና ማበርታት

- ወጎች

- ትምህርቶች

- ግጥሞች

፫. ሌሎች መጻሕፍት ክፍል።

- ሃይማኖተ አበው

- መጽሐፈ ስንክሳር

- ፍኖተ እግዚአብሔር

Meer InfoMinder Info

What's new in the latest 2.1

Last updated on 2020-11-09
Target API 29 (Android 10) updated

ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk APK -informatie

Laatste versie
2.1
Android OS
Android 4.0+
Bestandsgrootte
9.6 MB
Inhoudsbeoordeling
Everyone
Veilige en snelle APK Downloads op APKPure
APKPure gebruikt handtekeningverificatie om virusvrije ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk APK downloads voor u te garanderen.

Supersnel en veilig downloaden via de APKPure-app

Eén klik om XAPK/APK-bestanden op Android te installeren!

Downloaden APKPure