ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01)

ነቅረእ - 01 የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01)

  • 98.7 MB

    파일 크기

  • Android 4.1+

    Android OS

ነቅረእ - 01 የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 정보

ነቅረእ- 01 አፕልኬሽን ቁርኣን ውስጥ የዐረብኛ ፊደላትን በቀላሉ ማወቅና መለየት እንድንችል የሚያስተምር አፕልኬሽን

ነቅረእ-01 የሞባይል አፕልኬሽን በረጅም ጊዜ ጥናት በነቅረእ ዘመናዊ የቁርኣን ንባብ ት/ቤት የተዘጋጀ ቁርኣን ውስጥ የዐረብኛ ፊደላትን በቀላሉ ማወቅና መለየት እንድንችል የሚያስተምር እጅግ ዘመናዊ የሞባይል አፕልኬሽን ነው፡፡

አፕልኬሽኑ ለተጠቃሚዎች ምቹ እና ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ ተያያዥ በሆኑ አራት ክፍሎች ተከፍሏል፡፡

ክፍል አንድ፡ የዐረብኛ ፊደላትን በግርድፉ መለየት

በዚህ ክፍል ተጠቃሚው ከሀያ ስምንቱ የዐረብኛ ፊደላት ጋር የመጀመሪያ ትውውቅ ያደርጋል፡፡ እያንዳንዱ የዐረብኛ ፊደል የሚለይበት ነገራት ተጠቅሰው ፊደላትን በግርድፉ የመለየት ትምህርት በጥልቀት ይሰጣል፡፡ ይህ ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል ሀያ ስምንቱንም የዐረብኛ ፊደላት በግርድፉ ለመለየት በምስል ፡ በጽሑፍና በድምጽ በታገዝ ሁኔታ በደንብ የተብራራ ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ደግሞ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አስተማሪ ቪዲዮዎች ተካተዋል፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ሁለት ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ ቀጣይ ክፍል ሁለት ይከፈትሎታል፡፡

ክፍል ሁለት፡ የዐረብኛ ፊደላት የድምጽ አወጣጥ

በዚህ ክፍል የሀያ ስምንቱ የዐረብኛ ፊደላት የድምጽ አወጣጥ ትምህርት በዝርዝርና በጥልቀት ይሰጣል ፡፡ እያንዳንዱን የዐረብኛ ፊደል ከአማርኛ ፊደላት የድምጽ አወጣጥ ጋር በማነጻጸር ትክክለኛ የድምጽ አወጣጡን የማወቅና የማውጣት ትምህርት በጥልቀት ይሰጣል፡፡ ይህም ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል የሀያ ስምንቱን የዐረብኛ ፊደላት ትክክለኛ የድምጽ አወጣጥ በምስል፡ በጽሑፍና በድምጽ በታገዝ ሁኔታ በደንብ የተብራራ ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ደግሞ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አስተማሪ ቪዲዮዎች ተካተዋል፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ሶስት ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ ቀጣይ ክፍል ሶስት ይከፈትሎታል፡፡

ክፍል ሶስት፡ የዐረብኛ ፊደላት የአቀጣጠል ሁኔታ

በዚህ ክፍል ከሀያ ስምንቱ የዐረብኛ ፊደላት የአቀጣጠል ሁኔታና ቅርጽ ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ትምህርት ይሰጣል፡፡ እያንዳንዱ የዐረብኛ ፊደል የዐረብኛ ቃላት ውስጥ ተቀጣጥሎ በሚመጣበት ጊዜ እንዴት በቀላሉ መለየት እንደምንችል የሚያግዘን ትምህርት በስፋትና በጥልቀት ተካቷል፡፡ ይህም ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል ሀያ ስምንቱንም ፊደላት በዐረብኛ ቃላት ውስጥ ተቀጣጥለው ሲመጡ በቀላሉ የመለየት ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ደግሞ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አስተማሪ ቪዲዮዎች ተካተዋል፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ ቀጣይ ክፍል አራት ይከፈትሎታል፡፡

ክፍል አራት፡ የዐረብኛ ፊደላትን ውስጥ መለየት

በዚህ ክፍል ሀያ ስምንቱን የዐረብኛ ፊደላት ቁርኣን ውስጥ የመለየት ልምምዳዊ ት/ት ይሰጣል ፡፡ አንድ ከቁርኣን የተወሰደ ምዕራፍ ተጠቅሶ በዚያ ምዕራፍ ውስጥ የሚገኙትን የዐረብኛ ፊደላት ባለፉት ሶስት ክፍሎች በተማረው መሰረት ፊደላቱን ቁርኣን ውስጥ የመለየት ተግባራዊ የልምምድ ት/ት ይሰጣል ፡፡ ይህም ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል ሀያ ስምንቱንም የዐረብኛ ፊደላት በምሳሌነት በተሰጠው የቁርኣን ምዕራፍ ውስጥ በቀላሉ የመለየት ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ምንም ተያያዥ ቪዲዮ አልተካተተም፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ የዐረብኛ ፊደላት የማወቅና የመለየት ት/ት በአግባቡ መጨረስዎ እርግጥ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ :

Telegram: @neqra

Facebook: neqraquranreadingcenter

+251 911 38 39 49 /+251 911 55 56 76

더 보기

What's new in the latest 1.0

Last updated on 2019-03-15
- 1 Lesson free trial
더 보기

비디오 및 스크린 샷

  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 포스터
  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 스크린샷 1
  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 스크린샷 2
  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 스크린샷 3
  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 스크린샷 4
  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 스크린샷 5
  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 스크린샷 6
  • ነቅረእ - 01  የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) 스크린샷 7

ነቅረእ - 01 የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01)의 오래된 버전

APKPure 아이콘

APKPure 앱을통한매우빠르고안전한다운로드

한번의클릭으로 Android에 XAPK/APK 파일을설치할수있습니다!

다운로드 APKPure
thank icon
사용자 환경을 개선하기 위해 이 웹 사이트의 쿠키 및 기타 기술을 사용합니다.
이 페이지의 링크를 클릭하면 당사의 개인 정보 보호 정책쿠키 정책에 동의하는 것입니다.
더 알아보기