APKPure에서 안전하고 빠른 APK 다운로드
APKPure는 바이러스 없는 Arganon - መጽሐፈ አርጋኖን APK 다운로드를 위해 서명 확인을 사용합니다.
Arganon መጽሐፈ አርጋኖን የእመቤታችን ምስጋና (በአማርኛ)
Arganon - መጽሐፈ አርጋኖን የእመቤታችን ምስጋና
(በአማርኛ)
ምስጋና ጸሎትና መንበርከክ ላስታማሩኝ ለተከበሩ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ::
አርጋኖን የተሰኘው መጽሐፍ ሊቁ እመቤታችንን በቅኔ ያመሰገነበት መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ እንደ ውዳሴ ማርያምና እርሱ እንደጻፈው ኆኅተ ብርሃን በሰባት ቀን የተከፋፈለ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ አብዛኛውን ጊዜ በነግህ ጸሎት የሚደርስ ነው፡፡ ገዳማውያን አባቶች በስፋት ይገለገሉበታል /ይጸልዩበታል/ በዚህ መጽሐፍ እምቅነት እና ይዘት የተደሰቱት ዐፄ ዳዊት መጽሐፉ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አዘው እንደነበር ይነገራል፡፡ ስለ አርጋኖን ድርሰቱ እንደሚከተለው በገድሉ ተጽፏል፡፡ ‹‹ወሰመዮ በሠለስቱ አስማት ዘውእቶሙ አርጋኖን ውዳሴ ወመሰንቆ መዝሙር ወእንዚራ ስብሐት፤ በሦስት ሰዎችም ሰየማቸው እነርሱም አርጋኖነ ውዳሴ፣ መሰንቆ መዝሙርና እንዚራ ስብሐት ይባላሉ፡፡›› ይህ አገላለጥ አርጋኖን አንድ ሆኖ ሦስት መድብሎች ያሉት እንደሆነ ያሳያል፡፡