Over Gibre Himamat ግብረ ሕማማት
የግብረ ሕማማት መጽሐፈ ፣ መጽሐፈ ጾመ ድጓ እና የአጽዋማት ምንባባት
ይህ አፕሊኬሽን ሃምሳ ብር ያስከፍላል።
Gibre Himamat is een Ethiopisch Orthodox Tewahedo-boek dat wordt gelezen in de Heilige week, de laatste week van de vasten. Het boek bevat lezingen van Palmzondag, Heilige Maandag, Heilige Dinsdag, Heilige Woensdag (Spion Woensdag), Witte Donderdag (Heilige Donderdag), Goede Vrijdag (Heilige Vrijdag), Heilige Zaterdag en Pasen. Het boek bevat lezingen uit de Bijbel, orthodoxe canonieke boeken, synaxarium, wonderen van Jezus Christus, wonderen van Maria, profetieën, gebedenboeken, Haymanote Abew, Covenant Prayer, Gedles en meer Ethiopisch orthodoxe Tewahedo kerkboeken.
Het geheime doel van dit boek is om ons eraan te herinneren dat de Heer ons de pijn, de dood, de eeuwige vrijheid en heerlijkheid heeft gegeven in Zijn opstanding, en dat Hij de God van het leven is zonder pijn en dood, elke dag gelezen en gerepeteerd in deze heilige week
Dienovereenkomstig is het algemene patroon van het gebed en de dienst van de Gibre Himamat in dit boek vervat, en het is onze oprechte hoop dat de priesters en parochianen het boek kunnen vasthouden en volgen.
መጽሐፈ ግብረ ሕማማት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታችንነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀል የሚዘከርበትና በሰሙነ ሕማማት የሚነበብ ታላቅ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ፣ መጻሕፍት ፣ ከትንቢት ፣ ከድርሳናት ፣ ከተአምራት ፣ ከመዝሙራት ፣ ከተግሣጻት ፣ ከሃይማኖተ ከመጽሐፈ ስንክሳርና ከአበው መጻሕፍት የተውጣጡ ትምህርቶችንና የጸሎት ክፍሎችን ከሆሣዕና ዋዜማ እስከ ትንሣኤ ባሉት ስምንት ቀናንት በሰዓታት ተከፋፍሎ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።
የመሠረቱና ታሪካዊ አመጣጡም ከአባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ተያይዞ የመጣ ነው። ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለሐዋርያት እየተገለጸ እስከ አርባ ቀን ድረስ መጽሐፈ ኪዳንንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምራቸው ቈይቶ። በአርባ ቀኑም ሐዋርያትን በአንብሮተ እድ ሹሟቸውና ባርኳቸው አርጓል። (ማር ፲፮ ፲ህ። ሉቃ ፳፬ ፤ ፶፩። የሐዋ ሥራ ፩-፱)
ከዚህም በኋላ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ካሉ ምዕመናን ጋር ጾም መጾምንና ትንሣኤውን ማክበር ጀመሩ። ሕማማት ጊዜ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው በደነገጉት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ስለ ሰሙነ ሕማማት «ወአንትሙሰ ተዐቅቡ ወግበሩ ተዝካረ ሕማማቲሁእናንተ ግን ጠብቃችሁ የመከራ መስቀሉ መታሰቢያ የሆነውን ሕማማቱን አድርጉ አክብሩ» ሲሉ አዝዘዋል። (ትእዛዝ ፴፩)
ሆኖም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ይፋጠኑ ነበረና እንደ ዛሬው ሁሉ ጊዜውን አልወሰኑትም ነበር። ከሐዋርያት ቀጥለው የተነሱ ሊቃውንትም ቢሆኑ እንደዚሁ በዐተ ጾምን ከጥር ፲፩ ቀን እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ከጾመ። በኋላ ሰሙነ ሕማማትን ደግሞ ከዐቢይ ጾም ለይተው ከመጋቢት ፳፪ እስከ መጋቢት ፳፰ ቀን በመጾም መጋቢት ፳፱ ቀን ትንሣኤውን ያከብሩ ነበር። ይህ ሥርዓት ሲያያዝ እስከ ድሜጥሮስ ዘመን ደረሰ።
ከ፩፻፹፰ እስከ ፪፻፴ ዓ.ም የነበረው ሊቀ ጳጳስ ድሜጥሮስ በአዘጋጀው የጊዜ መቁጠሪያ (ባሕረ ሐሣብ) ሰሙነ ሕማማት ከዐቢይ ጾም ቀጥታ እንዲሆን ተወስኖአል። ቤተ ክርስቲያንም በቀመረ ድሜጥሮስ ዓመታትን በንዑስ ፤ በማዕከላዊና በዐቢይ ቀመር እየቀመረች አጽዋማት የሚገቡበትንና በዓላት የሚውሉበትን ጊዜ ለምዕመናን ታሳውቃለች።
ስለሆነም የሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎትና አገልግሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮት ጋር የተያያዘ ቢሆንም አሁን ያለውን ሥርዓት የያዘ ግብረ ሕማማት ፤ የተሰኘው መጽሐፍ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ የዋለው ከጌታ ልደት በኋላ በ፲፬ኛው ምዕት ዓመት ነው።
ከ፩ሺ፫፻፵ እስከ ፩ሺ፫፻፹ ዓ.ም የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ብርሃነ ዐዜብ ከዐረብኛ ወደ ግእዝ እንደተረጎሙት ቀደም ሲል በግእዝ ብቻ ታትሞ በነበረው የግብረ ሕማማት መጽሐፍ ውስጥ ተገልጦአል።
የመጽሐፉ ስያሜም ከጥንተ ስሙ ጀምሮ ግብረ ሕማማት እንደሚባል በመጽሓፉ ውስጥ በብዙ ክፍል ተጠቅሶ ይገኛል። ለዚሁም በቂ የሆነ ምሥጢራዊ ምክንያት እንዳለው ይታመናል።
ምሥጢራዊ ዓላማውም ጌታ በሕማሙ ሕማማችንን ፤ ሞታችንን ፤ በትንሣኤው ዘለዓማዊ ነፃነትንና ክብርን ያጐናጸፈን መሆኑን ከማስገንዘቡም በላይ በባሕርዩ መከራና ሞት የሌለበት ሕያወ ባሕርይ አምላክ መሆኑ በሰሙነ ሕማማት በየአንዳንዱ ቀን ይነበባል ይተረካልም።
በዚህ መሠረት የሰሙነ ሕማማት ጸሎትና አገልግሎት ጠቅላላ ሥርዓት በዚህ መጽሓፈ ግብረ ሕማማት በየክፍሉ ተጽፎ ስለሚገኝ ካህናትም ምዕመናንም መጽሐፉን በመያዝ ሥርዓቱን ለመከታተል ያመቻል የሚል ጽኑእ ተስፋ አለን።
What's new in the latest 4.0
Gibre Himamat ግብረ ሕማማት APK -informatie
Oude versies van Gibre Himamat ግብረ ሕማማት
Gibre Himamat ግብረ ሕማማት 4.0
Gibre Himamat ግብረ ሕማማት 3.0.1
![APKPure-icoon](https://image.winudf.com/v2/upload/images/icon.png/image.png?fakeurl=1&w=120)
Supersnel en veilig downloaden via de APKPure-app
Eén klik om XAPK/APK-bestanden op Android te installeren!