TMCCE የቦታ መረጃ በመሰብስብ የኮቪድ-19 መስፋፋትን ፣ መከታተል እና መቆጣጠሪን ያግዛል፡፡
TMCCE (Track, monitor and control COVID-19 Expansion) የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም የጉዞ መረጃዎን ይወስዳል በፈለጉት ጊዜም ማቃረጥ ይችላሉ፡፡ መተግበሪያ የቦታ መረጃዎን ለመመዘገብ የኢንተርኔት መረቭ አያስፈልገዉም፡፡ በተጨማሪ መተግበሪያዉን የሚጠቀመዉ ሰዉ ከዚህ በፊት የነበረዉን የጉዞ ታሪክ (መተግበሪያዉ እንዲመዘግብ የፈቀደዉን በቻ) በካርታ ለይ ያሳየዋል ፣ የሞባይል መተግበሪያ ጠተቃሚዉ ሰዉ እራሱን በ ኮቪድ 19 ቫይረስ ተጋላጭነት ከጠረጠረ አልያም በሆነ አጋታሚ ቫይረሱ እንዳለበት ባረጋገጠ ጊዜ እስካሁን በፍቃዱ የተመዘገበዉን የጉዞ መረጃ ለተዘጋጀዉ ማክከላዊ ኣካል ይልካል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በኢትዮጵያ በየት አካባቢ እየተስፋፋ እንደሆነ እና ተጠቃሚዉ በየተኛዉ አካባቢ የበለጠ ጥንቃቄ መዉስድ እንዳለበት እና የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶች ሪፖርት መመዝገብ ያስችላል፡፡