ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

  • 9.6 MB

    Dimensione

  • Android 4.0+

    Android OS

Informazioni su ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና በቅብዐት እምነት.

«ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ» በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ዶግማ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ከ፲፪ መጻሕፍት በላይ ተካተውበት የቀረበ የመጻሕፍት መድብል ነው።

ይህ የመጻሕፍት መድብል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትርጓሜ ሊቃውንት የተራቀቁባቸውን እና የተጠበቡባቸውን ሲወርዱ ሲወራረዱ ለእኛ የደረሱ የትርጓሜ መጻሕፍት የተካተቱበት ነው። በሦስት ዐበይት ክፍሎች የተመደቡ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ያካተተው ይህ መድብል ምክርና ተግሳጽንም የያዘ ስለሆነ ብዙዎች እንደሚወዱት ተስፋ እናደርጋለን። በአዘጋጁ ታትመው የቀረቡና እና ለኅትመት ዝግጁ የሆኑ መጻሕፍትም የተካተቱበት ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል። በአዘጋጁ ከቀረቡ መጻሕፍት መካከል በቅብዐት ምንፍቅና አማኞች ለተጻፉ መጻሕፍት ተገቢ ምላሽ የተሰጠባቸውን «ደብረ አሚን - የሃይማኖት ተራራ» እና «ፍኖተ ጽድቅ - የእውነት ጎዳና» አካተናል። ከዚህ በተጨማሪም አዘጋጁ የጻፋቸው የተለያዩ ወጎች ፣ ትምህርቶችና ግጥሞችም ምክርና ተግሳጽን በስፋት አካተው ቀርበውበታል። ከእግዚአብሔር ለምን እንርቃለን? እግዚአብሔርስ ከእኛ ለምን ይርቃል? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመልስ እና ወደ ንስሐ የሚመራ «ለምን ርቀህ ቆምህ?» የተሰኘው የአዘጋጁ መጽሐፍም በዚሁ መድብል ውስጥ የተካተተ ነው። እነዚህ የአዘጋጁ መጻሕፍት ገበያ ላይ የማይገኙ መሆናቸው ይህን መተግበሪያ ልዩ ያደርገዋል።

ይህ መተግበሪያ በተጨማሪነት ቤተ ክርስቲያናችን ከዓመት እስከ ዓመት የምትገለገልባቸውን ድንቅ መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውንና መጽሐፈ ስንክሳርን ያካተተ ነው።

ይህ መተግበሪያ የያዛቸው መጻሕፍት ዝርዝር

፩. የአንድምታ ትርጓሜ ክፍል

- የጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ።

-የውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።

- የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።

- የአራቱ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ።

፪. የአዘጋጁ መጻሕፍት ክፍል

- ደብረ አሚን

- ፍኖተ ጽድቅ

- ለምን ርቀህ ቆምህ?

- አማኞችን ማጽናትና ማበርታት

- ወጎች

- ትምህርቶች

- ግጥሞች

፫. ሌሎች መጻሕፍት ክፍል።

- ሃይማኖተ አበው

- መጽሐፈ ስንክሳር

- ፍኖተ እግዚአብሔር

Mostra Altro

What's new in the latest 2.1

Last updated on 2020-11-09
Target API 29 (Android 10) updated
Mostra Altro

Video e screenshot

  • Poster ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
  • 1 Schermata ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
  • 2 Schermata ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
  • 3 Schermata ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
  • 4 Schermata ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
  • 5 Schermata ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
Icona APKPure

Download super veloce e sicuro tramite l'app APKPure

Basta un clic per installare i file XAPK/APK su Android!

Scarica APKPure
thank icon
We use cookies and other technologies on this website to enhance your user experience.
By clicking any link on this page you are giving your consent to our Privacy Policy and Cookies Policy.
Learn More about Policies